ጌታ ቢፈቅድ
Gieta Bifeqd
2005 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከማመስገን ፈጽሞ እኔ አልቆጠብ
ልጅ ብቻ መሆኔ ይበቃኛል እርሱን ለማመስገን
አልናወጥ በሆነው ባልሆነው ነገር
እርሱ ያለው ይሆናል አንዳችም ሳይቀር (፫x)
እርሱ ያለው (አሃ) ጌታ ያለው (ኦሆ)
ውዴ ያለው (አሃ) አባ ያለው (ኦሆ)
እርሱ ያለው ይፈጸም ሌላው (፫x) ሌላው ከንቱ ነው
እርሱ ያለው ይፈጸም ሌላው (፫x) ሌላው አላፊ ነው
አዝማች · Chorus
ጌታ ቢፈቅድ ብንኖር
እንዲና እንዲያ እናደርጋለን
ብሎ ማረፍ መልካም ነው በርሱ መታመን
አያዋጣም መሯሯጥ እዚህም እዚያም ማለት (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም
ሁሉም ከንቱ ነው ከንቱ ከእግዚአብሔር በቀር
የተጣበቀ ከዚህ ጌታ ጋር ዘመኑ ሁሉ ይለመልማል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ ቢፈቅድ ብንኖር
እንዲና እንዲያ እናደርጋለን
ብሎ ማረፍ መልካም ነው በርሱ መታመን
አያዋጣም መሯሯጥ እዚህም እዚያም ማለት (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወደ ግራ እኔ ወደ ቀኝም አልል
በቀን በሌት አዎ ቃሉን ነው የማስብ
የዚያን ጊዜ መንገዴ ይቀናልኛል
የረገጥኩትን ሁሉ እርሱ ያወርሰኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ ቢፈቅድ ብንኖር
እንዲና እንዲያ እናደርጋለን
ብሎ ማረፍ መልካም ነው በርሱ መታመን
አያዋጣም መሯሯጥ እዚህም እዚያም ማለት (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ