ከዘመን ዘመን
Kezemen Zemen
2005 · ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ያው ነው እግዚአብሔር ያው ነው
ያው ነው ጌታዬ ያው ነው
ያው ነው ኢየሱስ ያው ነው
ያው ነው አምላኬ ያው ነው
ጥንትም የሚሰራ አሁንም ያው ነው
አልተለወጠም ኃይሉ ሙሉ ነው (፪x) (ሃሌሉያ)
ቁጥር 1 · Verse 1
ባህሩን በተዓምር የከፈለ
አንካሳውን ደግሞ ያዘለለ
እውሩን በእጆቹ ዳሰሰና
በሰላም ሂድ አለው ፈወሰና (፪x)
ጴጥሮስን በውሃ ላይ ያራመደ
ማዕበል ወጀቡን ጸጥ ያረገ
እንደሱ የሚሆን የትም የለም
ይባረክ ይመስገን ለዘላለም (፪x)
አዝማች · Chorus
ያው ነው እግዚአብሔር ያው ነው
ያው ነው ጌታዬ ያው ነው
ያው ነው ኢየሱስ ያው ነው
ያው ነው አምላኬ ያው ነው
ጥንትም የሚሰራ አሁንም ያው ነው
አልተለወጠም ኃይሉ ሙሉ ነው (፪x) (ሃሌሉያ)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምንም በሌለበት ምድረ በዳ
ሕዝቡን የሚመግብ የሚረዳ
በጠሩትም ጊዜ ከተፍ የሚል
የሚያኮራ ጌታ የሚያስተማምን
በጠሩትም ጊዜ ከተፍ የሚል
የሚያኮራ ጌታ የሚያስተማምን (፪x)
ዛሬም ለኔ (ዛሬም ለኔ) በዘመኔ (በዘመኔ)
ድንቅ አድርጐልኛል ኢየሱስ ጌታዬ (፪x)
አዝማች · Chorus
ያው ነው እግዚአብሔር ያው ነው
ያው ነው ጌታዬ ያው ነው
ያው ነው ኢየሱስ ያው ነው
ያው ነው አምላኬ ያው ነው
ጥንትም የሚሰራ አሁንም ያው ነው
አልተለወጠም ኃይሉ ሙሉ ነው (፪x) (ሃሌሉያ)
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል
ጥራኝ እኔ ደግሞ እሰማሃለሁ
የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገር አሳይሃለሁ
በቃሌ እኔ እተጋለሁ ድምጽህን ፈጥኜ እሰማለሁ
ከቃሌ ጋራ እሆናለሁ ብቻ አንተ እመን እሰራለሁ (፪x)
ዛሬም ለኔ (ዛሬም ለኔ) በዘመኔ (በዘመኔ)
ድንቅ አድርጐልኛል ኢየሱሱ ጌታዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ