እግዚአብሔር አንተ
Egziabhier Ante
2005 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔርን አንተ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ
አምባዬና መሸሸጊያዬ ነው ፣ ኢየሱስ በእርሱ እታመናለሁ
ኢየሱሴን ኢየሱሴን በጣም እወደዋለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም አድኖኛል
እውነት እንደጋሻ ሆኖ ዙሪያዬን ከቦኛል
መድኃኒት መድኃኒት እርሱ ሆኖልኛል (፪x)
በቀንም ከሚበር ከሌሊትም ግርማ አድኖኛል
በመንገዴ ሁሉ ስለኔ መላእክቱ ታዘዋል
ጥበቃው ጥበቃው እንዴት ያስተማምናል (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔርን አንተ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ
አምባዬና መሸሸጊያዬ ነው ፣ ኢየሱስ በእርሱ እታመናለሁ
ኢየሱሴን ኢየሱሴን በጣም እወደዋለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በተኩላና በእባብ ላይም እጫማለሁ
አንበሳ ዘንዶውን እረጋግጣለሁ
በርሱ ተማምኜ ሁሉንም አልፋለሁ
ስሙንም ደግሜ ደግሜ እጠራለሁ (፪x)
ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)
ኢየሱስ በጣም እወደዋለሁ ኢየሱስ
ኢየሱስ በጣም እወደዋለሁ ኢየሱስ
ሃሌሉያ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ