ይገርማል
Yegermal
2005 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምንም ክፍያ አልከፈልኩም
ከላይ ወደታችም አላልኩም
በጓደኛም ዘመድ አልመጣሁም
ጌታን ለማግኘት አልደከምኩም
በፍቅር ቃሉ ሲናገረኝ
እወድሃልሁ ብሎ ሲለኝ
እጅግ ተገረምኩ ተደነቅኩ
እንዲህ ያለ ሰው ማነው አልኩ
ያለ የነበረ የሚኖረው
ኤልሻዳዩ ጌታ ለካስ (፫x) ለካስ ኢየሱስ ነው
ሁሉን ቻይ ጌታ ለካስ ለካስ ኢየሱስ ነው
ይገርማል ኧረ እንዴት ይገርማል
ይደንቃል ኧረ እንዴት ይደንቃል
ሳልመርጠው ኢየሱስ መርጦኛል
ሳልወደው እንዲህ ወዶኛል
ከሞት መካከል ነጥቆ አውጥቶኛል
አዝማች · Chorus
ሳመሰግነው ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
ስዘምርለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
እልል ስልለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
ያደረገልኝን እያየሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
አምኜ በድንገት ያገኘሁት
ሕይወቴን ሁሉ የሰጠሁት
ይኸው እስካሁን ይመራኛል
ደግሞም ዘላለም ያኖረኛል
ከእጆቹ መሃል ማን ያወጣኛል
ከእጁ ፈልቅቆ ማን ይወደኛል
ይበልጣል ከሁሉም ይበልጣል
ይመረጣል ኢየሱሴ ይመረጣል
መች አሳልፎ ይሰጣል ስሙ ከስሞች ይበልጣል
ኢየሱን ጠርቶ ማን አፍሮ ያውቃል
አዝማች · Chorus
ሳመሰግነው ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
ስዘምርለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
እልል ስልለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
ያደረገልኝን እያየሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የክብር ጌታ ድንቅ አረገ ፣ አቤት ዲያቢሎስ ተናደደ
ውስጠ ሚስጥሩም ተገለጠ ፣ የጋረደውም ተቀደደ
አሁን ምን ይበል ምን ይዋጠው
ኢየሱስ ማንነቱን ሲገልጠው (፪x)
ይነድዳል እሳቱ ይነድዳል ፣ ይዋረዳል ዲያቢሎስ ይዋረዳል
መች በዚህ ብቻ ያበቃል ፣ የያዘውን ሁሉ ይለቃል
ማሳወር እንጂ እሱ ማብራት የት ያውቃል
ማዋረድ እንጂ እሱ ማክበር የት ይውቃል
አዝማች · Chorus
ሳመሰግነው ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
ስዘምርለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
እልል ስልለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ
ያደረገልኝን እያየሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እስኪ እንደኔ ጌታ የሰራላችሁ
በምድረ በዳ ውሃ የሰጣችሁ
ይሰማ ዛሬ እልልታችሁ
ፈጽሞ አይቆጠብ ድምጻችሁ (ፈጽሞ አይቆጠብ ድምጻችሁ)
እስኪ እንደኔ ጌታ የሰራላችሁ
በጨለማ ውስጥ ብርሃን የሆናችሁ
ይሰማ ዛሬ እልልታችሁ
ፈጽሞ አይቆጠብ ድምጻችሁ (ፈጽሞ አይቆጠብ ድምጻችሁ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ