Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስላንተ ቢወራ

Selante Biwera

2005 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስላንተ ሲወራ ሲነገር ቢዋል ቢታደር

የሚበቃ አይደለም ብዙ ነው ያረከው ነገር

እንዲሁ ብቻ ልበል ተመስገን

ቃላት አይገልጸውም ያረከውን ነገር (፪x)

ሞቴ በሕይወት ተቀይሮልኛል ኑር ብለህ ፈቅደህልኛል

በምድር በርዝመቷ በስፋቷ በላይ በላይ በከፍታ

እንድወጣ እንድገባ ፈቅደህልኛል

የሚይዘኝ የለም ከፊቴ ወጥተህልኛል (፪x)

ስላንተ ሲወራ ሲነገር ቢዋል ቢታደር

የሚበቃ አይደለም ብዙ ነው ያረከው ነገር

እንዲሁ ብቻ ልበል ተመስገን

ቃላት አይገልጸውም ያረግከውን ነገር (፪x)

አርነት ነፃ ወጥቻለሁ እርሱ ለቅቆኝ ተለቅቄያለሁ

አልሄድ ወደኋላ ወደፊት እራመዳለሁ

እርሱ ከከፈተው አትገባም የሚለኝ ማነው

ሸክሜን ጣለ ቀንበሬን ሰበረ ፣ እዳዬም በርሱ ተከፈለ

አለኝ አልጥልህም አልተውህም ፣ ፍጹም ከእጄ አላወጣህም

መርጬሃለሁ ምንም ነገር አያስፈራህም

ስላንተ ሲወራ ሲነገር ቢዋል ቢታደር

የሚበቃ አይደለም ብዙ ነው ያረከው ነገር

እንዲሁ ብቻ ልበል ተመስገን

ቃላት አይገልጸውም ያረከውን ነገር (፪x)

እየገባኝ መጣ አሁን እየተረዳሁ ፣ ነገሬ ሁሉ ባንተ ሰምሮ እያየሁ

አጋጣሚ አይደለም ለካ ከላይ ታዞ ነው

አርፌ እንድኖር ቀድሞ ስራዬን ሰርቶት ነው

ከተመስገን ሌላ ታዲያ የምለው ምንድነው

ተመስገን (፬x)

የኔ ጌታ ተመስገን

ተመስገን ላረግክልኝ ነገር (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ