በመጀመሪያ
Bemejemeria
2005 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በመጀመሪያ በመጀመሪያ (፫x)
እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ነው (፫x)
ሌላው ተከታይ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሳይወድ በግዱ ይመጣል
የልቤ መሻት ይሆናል
እንደተጻፈው አደርጋለሁ
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ነው (፪x)
ሰው ባለው በሃብቱ ምን ቢኮራ
ቢማር ሊቅ ቢሆን ታሪክ ቢሰራ
ጌታ ከሌለው ግን ባዶ ነው
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ነው (፫x)
ሌላው ተከታይ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዳዊትም ኖረ እድሜ ዘመኑን
መጀመሪያ አርጐ እግዚአብሔርን
የሚቋቋመው አልነበረም
መንግስቱ ጸና ለመለመ
የእግዚአብሔር ልቡ እንዳረፈበት
እንደልቤ እንዳለው እንደኮራበት
እንደእምነት አባቴ እንደዳዊት
አስደስታለሁ የጌታን ልብ
አዝማች · Chorus
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ነው (፫x)
ሌላው ተከታይ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ