አቤቱ በዘመናት
Abietu Bezemenat
ትራክ 3 · 4:48 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል
ብቻህን ስራህን ሰርተህ
ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (፪x)
በዘመን በአመታት ስራህን እየሰራህ
የሚቃወምህ ሳይኖር ክንድህን እየገለጥክ
ልጆችህን ከድል ወደ ድል እያሸጋገርካቸው
የጠላታቸውን ሰፈር ይታያል . (1) . ወርሰው
አዝማች · Chorus
አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል
ብቻህን ስራህን ሰርተህ
ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፈርዖን ለዘመናት ሲያስጨንቅ ልጆችህን
ሕዝቤን ልቀቅ ስትለው ትዕቢት አርጐ ሲፋንን
በመጨረሻ ጌታ የግብጽን በኩር ገድለህ
ህዝብህን ነጻ አውጥተህ ጠላትን . (1) . ጥለህ
አዝማች · Chorus
አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል
ብቻህን ስራህን ሰርተህ
ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሁልጊዜ ሃሳብህን የልብህንም ፈቃድ
ታከናውነዋለህ በምትወደው መንገድ
በጐና ደስ የሚያሰኝ ግሩምና ድንቅ ነው
አምላካችን እግዚአብሔር አንተ የምታደርገው
አዝማች · Chorus
አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል
ብቻህን ስራህን ሰርተህ
ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ክብርህ ሰማያትንና ምድርን ሁሉ ሸፍኗል
በምክርህ በመንገድህ አንተን ማን ያክልሃል
ውበትህ ከፀሐይ ይልቅ እጅግ እጅግ ይደምቃል
ፍጥረት በሙሉ ይህን እያየ ያከብርሃል
አዝማች · Chorus
አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል
ብቻህን ስራህን ሰርተህ
ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ
ቁጥር 5 · Verse 5
ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ