Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታ ኤልሻዳይ ነው

Gieta Elshaday New

ትራክ 6 · 7:08 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ

በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ

ጌታ ኤልሻዳይ ነህ

ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (፪x)

ምድራችንን ጐበኘሃት ምህረትን ለእርሷ አደረግህ

ብልጽግናዋን አበዛህ ምግቧን አዘጋጅተህ ሰጥተህ

. (1) . በማስተካከል እውነት እያለስለስካት

ቡቃያውን በመባረክ መልካም ፍሬን አጠገብካት (፪x)

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ

በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ

ጌታ ኤልሻዳይ ነህ

ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (፪x)

ከክብርህ ባለጠግነት ነፍሳችንን እያጠገብክ

እስከ ሺ ትውልድ በሆነው በረከትህ እየባረክ

ሁሉን ለእኛ ሰጥተኸናል የረገጥነውን ወርሰናል

በስምህ ስልጣን በኃይልህ ሮሆቦት አሜን ሰርተናል (፪x)

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ

በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ

ጌታ ኤልሻዳይ ነህ

ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (፪x)

የምድርን አፈር ባርከኸው ሰብልን ይሰጣል ዛሬ

ጠግበን ረክተን እንኖራለን ለቅሷችን ሆኗል ዝማሬ

ወራት አመት ዘመናትን ለልጆችህ ተሰጥተዋል

ኤልሻዳይ ንጉሥ አንተ ነህ ሁሉን አቀዳጅተኸናል (፪x)

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ

በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ

ጌታ ኤልሻዳይ ነህ

ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (፪x)

የምድረበዳ ተራሮች በመንፈስ እውነት ረክተዋል

ኮረብቶችም በደስታ በስምህ ሀይልን ታጭቀዋል

የማሰማሪያ ቦታዋች በመንጐቹ ውበት ለበሱ

ሸለቆ እህል ተሞልቶ ክበር/ድመቅ ይልሃል ንጉሡ (፪x)

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ

በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ

ጌታ ኤልሻዳይ ነህ

ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ