Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቅዱስ ቅዱስ

Qedus Qedus

ትራክ 7 · 6:03 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ለሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር (፪x)

በነጩ ዙፋን ተቀምጠሃል

አክሊላቸውን ያወሩልሃል

ሁሉን ፈጥረሃል ፈቃድህ ሆኗል

እጅግ ትልቅ ነህ ማን ይመስልሃል

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ለሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር (፪x)

መልክህ እንዲህ ነው አንተ ትልቁ

. (1) .

ቀስተደመና ማዕረግህ ዙሪያህ

ከቦ ይልሃል ኃያል ቅዱስ ነህ

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ለሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር (፪x)

እልፍ ጊዜ እልፍ ሺህም ጊዜ ሺህ

የምትመለክ በመላእክትህ

በኪሩቤል ላይ ምትመላለስ

እግዚአብሔር አምላክ ዘላለም ቅዱስ

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር (፪x)

ነገሥታት ሲያልፉ ሲለዋወጡ

አንተ ግን ሕያው ሁልጊዜ ብርቱ

በቅንድቦችህ ሰውን መርማሪ

መሳይ የሌለህ ተወዳዳሪ

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር (፪x)

ከእስራት ፈቺ ቀንበር ሰባሪ

በጽድቅ ዙፋን ዘላለም ኗሪ

ማደሪያህ ቅዱስ አንተ ቅዱስ ነህ

ሰማይ ምድር ሲያልፍ በክብር አለህ

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

ቅዱስ (፬x) ኃያል (፬x)

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ