እምቢ ብዬ
Embi Beyie
ትራክ 5 · 4:07 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እምቢ ብዬ ሰይጣንን ከድቼው መጥቻለሁ
በኢየሱስ ጸንቼ ለመቆም መርጫለሁ
አልመኝም አንዳች አልፈልግም በሕይወቴ
ይበቃኛል የመስቀሉ ወዳጅ መድህኔን እዤ
አዝማች · Chorus
ከእርሱ ውጪ አልመኝ
አንዳች ነገር አያምረኝ
መጥቻለሁ በፍቅር
ለዘላለም ለመኖር (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙ ወዳጅ ማከማቸት ከንቱ ነው ያጠፋል
ለሁለት ጌቶች መገዛትም ደግሞ ሁሉን ያሳጣል
እኔስ በቃኝ እንድ ወዳጅ አለኝ ኢየሱሴ
በዚች ዓለም የተጐሳቆለው ስለነፍሴ
አዝማች · Chorus
ከእርሱ ውጪ አልመኝ
አንዳች ነገር አያምረኝ
መጥቻለሁ በፍቅር
ለዘላለም ለመኖር (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍቅሩ የእውነት የማይለዋወጥ እጅግ የጸና
በምህረቱ ሰውን የሚያቆመው ለምሥጋና
ዛሬ ይኽው እኔም ተመርጨ ዕጣው ደርሶኝ
ወደቤቱ መጣሁኝ ለክብሩ ቅኔን ልቀኝ
አዝማች · Chorus
ከእርሱ ውጪ አልመኝ
አንዳች ነገር አያምረኝ
መጥቻለሁ በፍቅር
ለዘላለም ለመኖር (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የዚህን ዓለም ብልጽግና ክብር ላልመኘው
ጊዜያዊውን የሚያልፈውን ነገር ላልፈልገው
ወስኛለሁ መርጫለሁ ጌታ ይሻለኛል
ለዘላለም . (1) .
አዝማች · Chorus
ከእርሱ ውጪ አልመኝ
አንዳች ነገር አያምረኝ
መጥቻለሁ በፍቅር
ለዘላለም ለመኖር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ