ወንድሜ ንቃ
Wendemie Neqa
ትራክ 9 · 6:31 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ወንድሜ ንቃ አትተኛ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ (፪x)
ጌታ እንደ ሌባ ይመጣልና
ቀን . (1) . አታውቅምና
ስለዚህ ንቃ መብራትህ ይብራ
በፍጻሜው ቀን እንዳትፈራ
አዝማች · Chorus
ወንድሜ ንቃ አትተኛ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ (፪x)
ስሙን በመፍራት ለሚኖሩት
የጽቅድ ጸሃይ ይወጣል በእውነት
እምላክህን ፍራ ጠብቀው ተግተህ
በክብር ሲገለጥ እንዳያፍርብህ
አዝማች · Chorus
ወንድሜ ንቃ አትተኛ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ (፪x)
ከማያምኑ ጋር ህብረት አይኑርህ
በማይመችህ መንገድ አትሂድ
ይልቅ ዘመኑን መርምር አጥብቀህ
በከንቱ አንዳያልፍ ጐልማሳነትህ
አዝማች · Chorus
ወንድሜ ንቃ አትተኛ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ሰዓቱ የመገለጡ (፪x)
እርሱን ከሚሉ ጋር ደስ ይበልህ
ከሰው ሁሉ ጋር ሰላም ይኑርህ
እጅጉን ንቃ ጊዜው ተቃርቧል
አሜን ይሆናል በርግጥ ይመጣል
አዝማች · Chorus
ወንድሜ ንቃ አትተኛ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ (፪x)
ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ
ኢየሱስ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ