Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታ ውድ ምህረትህ

Gieta Wed Mehereteh

ትራክ 8 · 5:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

ቸርነትህ ምህረትህ በሕይወት ዘመኔ

ስለሚጠብቁኝ በመሆን ከጐኔ

አልጠፋሁም ኢየሱስ አለሁኝ በቤትህ

ስዘምር እኖራለሁ ለታላቁ ስምህ

ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

ጠላቴ ሊያጠፋኝ ጦሩን ሲወረውር

ከግድግዳ ጋርም እኔኑ ሊያጣብቅ

ነገር ግን አልሆነም ምህረትህ ቀደመ

የዲያብሎስ ሃሳብ እቅዱ ባከነ

ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

በምህረትህ ብዛት ቤትህ እገባለሁ

አምልኮ ዝማሬ ስግደት እየሰጠሑ

ገናም እኖራለሁ ስለምትጠብቀኝ

እስከ ዓለም ፍጻሜ ሰለማትተወኝ

ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

አግዚአብሄር ታላቅ ባለብዙ ምህረት

ልጅህ ስላረከኝ በብዙ ቸርነት

እኔም በዝማሬ ምህረትህን አነግራለሁ

እስከምትወስደኝ አገለግላለሁ

ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

በልዑል መጠጊያ ሁሉን በምትችለው

ባንተ ስለምኖር ምህረትህ በበዛው

የሚያስፈራኝ የለም ከጠላትህ መንደር

አንተ ስለጣልከልኝ ወደ ጥልቁ ባሕር

ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

ኢየሱስ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

ልዑል ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ

ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ