ለእኔ ያለህ ፍቅር
Lenie Yaleh Feqer
ትራክ 2 · 6:48 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው
ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው
አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል
እንዴት ሊነገር ይችላል
በምን ሊገለጽ ይችላል
ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
መስቀል ተሸክመህ ደፋ ቀና ብለህ
በፈጠርከው ፍጥረት እየተንገላታህ
እጅጉን ተንቀህ በጣምም ተዋርደህ
እኔን አድነሃል ይግነን ታላቅ ስምህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው
ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው
አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል
እንዴት ሊነገር ይችላል
በምን ሊገለጽ ይችላል
ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ለአይምሮ በሚክብድ በዘግናኝ ሁኔታ
እጅህና እግርህ በሚስማር ተመታ
ያለ እንዳች ርህራሄ ኢየሱስ በጭካኔ
ግፍ አደረሱብህ ተሰቃየህ ለእኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው
ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው
አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል
እንዴት ሊነገር ይችላል
በምን ሊገለጽ ይችላል
ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ከወንበዴዎች ጋር ሰቀሉህ ኢየሱስ
ከላይ የወረድህ ሳለህ የዓለም ንጉስ
ሆምጣጤም አጠጡህ ጨከኙ በብዙ
ጌትነትህ የታል እያሉ እያፌዙ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው
ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው
አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል
እንዴት ሊነገር ይችላል
በምን ሊገለጽ ይችላል
ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
በእንጨት ተሰቅለህ እንደ መርገም ሰው
ለጠላቶችህ ማለድኽ ፍቅርህ ሰፊ ነው
ተፈጸመም አልህ ነፍስህን ሰጠህ ለኔ
ከፍ በል ተባረክ ዘላለም መድህኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው
ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው
አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል
እንዴት ሊነገር ይችላል
በምን ሊገለጽ ይችላል
ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ