መስቀሉ በፊቴ
Mesqelu Befitie
ትራክ 4 · 7:15 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴ እንዳይላላ
ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (፬x)
የቀራንዮን በግ ኢየሱስን ይዣለሁ
በሁለንተናዬ ላይም ሾሜሃለሁ
አልፈራም አልሰጋም ወጥቼ እገባለሁ
ዓለምን ሰይጣንን ስልጣኑን ክጃለሁ
አዝማች · Chorus
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ቁጥር 2 · Verse 2
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴ እንዳይላላ
ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (፬x)
ይህ የመስቀሉ ቃል በዓለም ለሚኖሩት
ከሞኝነት ውጭ አልሆነም ለሕይወት
ለእኔ ለምድን ግን በርታት ሆኖልኛል
የተሰራው ስራ ሕያው ሰው አርጐኛል
አዝማች · Chorus
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ
ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (፬x)
ሁሉን ፈጽማችሁ በፊቱ ለመቆም
የእምነትን ጋሻ ታጠቁ ልበሱ
የሚልን የድል ቃል ይዤ ልትጋ ልሩጥ
ጠፍቶ ከሚያጠፋ ከዚህ ዓለም ለማምለጥ
አዝማች · Chorus
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ቁጥር 4 · Verse 4
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ
ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (፬x)
ስለዓለም ሃጥያት ነፍሱን የሰጠውን
መከራና ስቃይ የተቀበለውን
እገሰግሳለሁ ታምኜው ከልቤ
እያገለገልኩት በፍፁም ሃሳቤ
አዝማች · Chorus
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ
መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ
ቁጥር 5 · Verse 5
ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ
ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ