አለኝ ብዙ ምሥጋና
Alegn Bezu Mesgana
ትራክ 1 · 5:09 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አለኝ ብዙ ምሥጋና ለአንተ
አለኝ ብዙ ምሥጋና
አምላኬ ነህና
እጅህ ሰርታኛለች ተመስገን
እፍ ብለህብኝ እስትንፋስህን
ሕያው ነፍስ ያለብኝ አደረከኝ
ተመስገን አምላኬ አበጀኽኝ
በእናቴ ማህጸን ገና ሳለሁ
በአንተ በአምላኬ ተለየሁ
ሳላውቅህ አውቀኸኝ ላዳንከኝ
ለውለታህ ብዙ ምሥጋን አለኝ
በመሰዋት ጻድቁን ልጅህን
ገለጽክልኝ እኔን መውደድህን
የእዳ ጽህፈቴን ደምስሰኽው
ሕይወቴን የሞላው ምሥጋናህ ነው
ህልናዬን በደምህ ቀድሰህ
መንፈስክህ ሞላኸኝ እንዳመልክህ
በቅዱሳን መሃል አቁመኸኝ
የከበረን መዝሙር አዘመርከኝ
በሥጋዬ ከከበኝ ሃጥያት
አስጣልከኝ አድርገህልኝ ምህረት
ታማኙና ኃይለኛው ክንድህ
ታድጐኛልና ላመስግንህ
በራሴ ስራ እኔን እያሳፈረክ
ሽታዬን ጠረኔን እየቀይርክ
በቃልህ ሰይፍ እየቆረጥከኝ
ያለጠባስ ቁስሌን ፈወስከኝ
አዝማች · Chorus
አለኝ ብዙ ምሥጋን ለአንተ
አለኝ ብዙ ምሥጋና
ሰሪዬ ነህና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ