ምን ያሻኛል
Men Yashagnal
ትራክ 8 · 5:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ለኔ ሁሉን ነው
ጌታዬ እርሱ በቂ ነው
የሚያሻን የለም ጌታ አለኝ
ሁሉ በሁሉ የሆንልኝ
ምን ያሻኛል ምን ያሻኛል ምን ያሻኛል
ጌታ ይበቃኛል
ምን እሻለሁ ምን እሻለሁ ምን እሻለሁ
ጌታን እግኝቻለሁ
የሰማይ የምድር ጌታ
በኃይሉ እጅግ የበረታ
ኢየሱስ ነው ለኔ የተሰጠኝ
በረከት ሙላት የሆንልኝ
ብሩና ወርቁም የእርሱ ነው
አምላኬ ሁሉን የፈጠረው
እንደ ፈቃዱ የሆነው
የአባቴ ፈቃድ ለኔ ነው
የእርሱ የሆነው የእኔ ነው
ወራሽ ነኝ ጌታ አባቴ ነው
እንደ ባሪያ ሳሆን እንደ ልጅ
ተቀብሎኛል እንደ ወዳጅ
አዝማች · Chorus
ለዚህ ጌታ እዜማለሁ
በመንፈሥም እቀኛለሁ
ለእርሱ ክብር ለእርሱ ምሥጋና
ይኸው መዝሙር ታላቅ ነውና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ