ውለታው አምላኬ
Weletaw Amlakie
ትራክ 11 · 6:12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ውለታው አምላኬ ለኔ ያደረገው
አያልቅም ባወራው ከእምሮ በላይ ነው
ተመስገን ልበለው
በምድር ላለው ለእንዳዱ ሰው ግድ የተሰኘው
ራሱን ለዓለም ቤዛ አድርጐ እንዲሁ የሰጠው
ለጠሉትና ላልተቀበሉት ሆኖ መስቀል ላይ
የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቀር በል አባት ሆይ
አዝማች · Chorus
ያለው ይሄ ጌታ ምን ዓይነት ፍቅር ነው
ምንስ ዓይነት ቋንቋ ይችላል ሊገልጸው
በምድር ካሉ ከተዋረዱ ከድሆች በላይ
ኢየሱስ ስለእኛ ቤዛ ሆነልን መጥቶ ከሰማይ
የሁላችንን በደልና ኃጢአት ተሸከመልን
እዳችንን እርሱ ከፍለ ነጻም አወጣን
ቁጥር 2 · Verse 2
በፍፁም ልባችን ጌታን ብንወደው
አይገባውም ወይ ለእኛ ላደረገው
መች በዚህ ብቻ በዚህ አበቃ የኢየሱስ ፍቅር
ከእርሱ ጋራ ወራስህ አረገን አብሮን የምኖር
የእርሱ የሆነውን አንዳችም ሳይቀር ለእኛ ሰጠው
ባርኮቱን ሁሉ ምንም ሳይሰስት ለእኛ አፈሰሰው
ታዲያ ለዚህ ጌታ ለእርሱ ብኖርለት
ይገባዋል እንጂ መች በዛበት
አዝማች · Chorus
ይህንን ውለታ የዋልልን ኢየሱስ ይመጣል
በዚህች ምድር ላይ ናፍቀን እንቀርም መጥቶ ይወስደናል
ወዳችንን በዓይናችን እናዋለን
ወድቀን ከእግሩ ስር እንወድሃለን እንለዋለን
ከተስፋ ሁሉ በላይ የተባረከው ተስፋችን
ጌታ ኢየሱስ ነው ስናየው ባይናችን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ