ተመሥገን ነው ያለኝ
Temesgen New Yalegn
ትራክ 9 · 4:07 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተመስገን ነው ያለኝ ለዚህ ለጌታዬ
እለት እለት በዝቷል ምህረቱ በላዬ
ተመስገን ነው ያለኝ ለዚህ ለጌታዬ
እለት እለት በዝቷል ምህረቱ በላዬ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለዚህ ሁሉ ሰላም ለዚህ ሁሉ እረፍት
አንድም ነገር የለም እኔ የከፈልኩት
የሰጠኸኝ ሁሉ ተገብቶኝ አይደለም
ምህረትህ በዝቶ ነው ክበር ለዘላላም
ቅዱሱ እግዚአብሔር ሆንህ ከኔ ጋራ
ከቅዱሳንም ጋር አረከኝ ምጠራህ
ለዚህ ያደረሰከኝ ኧረ እኔ ማን ነኝ
ምረትህ በዝቶ ነው ጌታ ክብረልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ ሆይ ምን አለ የሚያስደንቅ ነገር
አንተ ከሰው ጋራ ከመሆንህ በቀር
ምታስፈልገውን አንድም የሆንከውን
አምላኬ ተመስገን አግኝቻለሁ አንተን
በስምህ ባሕሩን ከፍለህ አሻግረኸኛል
ከጠላትም ወጥመድ አስመልጠኸኛል
እዚህ የደረስኩት በአንተ ጥበቃ ነው
ለበዛው ምህረትህ ምሥጋናዬ ይኸው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ