መንገድ አለው ጌታ
Menged Alew Gieta
ትራክ 6 · 5:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መንገድ አለው ጌታ እርሱ መንገድ አለው
መንገድ አለው ጌታዬ እርሱ መንገድ አለው
መንገድ አለው ጌታ እርሱ መንገድ አለው
መንገድ አለው ጌታዬ እርሱ መንገድ አለው
ቁጥር 2 · Verse 2
ባሕርን የሚከፍል ንፋስን ያመጣል
ውሃውን አስወግዶ መንገድ ያደርገዋል
ኃይለኛውንም ወንዝ እርሱ ያቆመዋል
ደርቅ መንግድ አድርጐ ማሻገር ይችላል
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም
ኤልሻዳይ ነው የሚሳነው የለም
ቁጥር 3 · Verse 3
ተራራውን አዞ ይደለድለዋል
ሸለቆውን ከፍ አድርጐ መንገድ ያደርገዋል
ቁጥር 4 · Verse 4
የእግዚአብሔር መንገድ በቀን ብቻ አይደለም
ሌሊቱም በእርሱ ዘንድ ጨለማ አይሆንም
በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም
ኤልሻዳይ ነው የሚሳነው የለም
ቁጥር 5 · Verse 5
ደመናም ባይታይ ነፍሱም ባይነፍስም
ለመጽናናት የሚሆን ምልክት ባይኖርም
መንገድ አለው ጌታ ውሃውን ያመጣል
የሌለውን ጠርቶ ማኖር ያውቅበታል
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም
ኤልሻዳይ ነው የሚሳነው የለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ