እንዳንተ ያለ አምላክ
Endante Yale Amlak
ትራክ 5 · 5:41 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ራስህን መስዋት አርገህ ስለእኛ ታርደሃል
ለአምላክህ አዲስ ሕዝብን በደምህ ዋጅተሃል
መንግሥትና ካህናት ለአባትህ አዘጋጀህ
አምልኮ ውዳሴ ምሥጋና ይብዛልህ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ይብዛልህ አምልኮ ይብዛልህ
ሌላማ ምን አለ ለአንተ የሚሰጥህ
ቁጥር 2 · Verse 2
እንዳተ ያለ አዳኝ አልተገኘምና
ኢየሱስ ሆይ ይብዛልህ አምልኮ ምሥጋና
ይገባሃልና
ቁጥር 3 · Verse 3
ከንፈሮችህ ጠቢብ በዕውቀት የላቁ
ጻድቅ ሆይ በዕውቀትህ ብዙዎች ጸደቁ
ለእግዚአብሔር ማደሪያ ቤትን ሰራህለት
አብም በአንተ ስራ ደስ ተሰኘበት
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ይብዛልህ አምልኮ ይብዛልህ
ሌላማ ምን አለ ለአንተ የሚሰጥህ
ቁጥር 4 · Verse 4
እንዳተ ያለ ጥቢብ አልተገኘምና
ኢየሱስ ሆይ ይብዛልህ አምልኮ ምሥጋና
ይገባሃልና
ቁጥር 5 · Verse 5
ነግስታት ኃያልን ጠቢባንም ጭምር
ጌታ ዝቅ በለው ይስጡ ለአንተ ክብር
ጐልማሶች ቆንጆዎች ሽማግሌዎች ይምጡ
ለታላቅነትህ ክብርን ለአንተ ይስጡ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ይብዛልህ አምልኮ ይብዛልህ
ሌላማ ምን አለ ለአንተ የሚሰጥህ
ቁጥር 6 · Verse 6
እንዳተ ያለ ጌታ አልተገኘምና
ኢየሱስ ሆይ ይብዛልህ አምልኮ ምሥጋና
ይገባሃልና
ቁጥር 7 · Verse 7
ከመላእክት በላይ ከነቢያት በላይ
ከሊቀ ካህናት ከአባቶችም በላይ
ተሹመህ በአብ ቀኝ ኢየሱስ ተቀምጠሃል
አምልኮ ውዳሴ ስግደት ይገባሃል
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ይብዛልህ አምልኮ ይብዛልህ
ሌላማ ምን አለ ለአንተ የሚሰጥህ
ቁጥር 8 · Verse 8
እንዳተ ያለ አምላክ አልተገኘምና
ኢየሱስ ሆይ ይብዛልህ አምልኮ ምሥጋና
ይገባሃልና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ