የምትረዳ የምታስደግፍ
Yemetreda Yemetasdegef
ትራክ 3 · 5:28 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የምትረዳ የምትደግፍ
የምታጽናና የምታሳርፍ
የማትለወጥ ሁሌ እውነተኛ
አንተ ነህ ኢየሱስ ለኔ ጋደኛ
ወዳጅ እንዳንት የለም
ክብር ለዘለዓለም
ወዳጅ እንዳንት የለም
ክብር ለዘለዓለም
ቁጥር 2 · Verse 2
የልቤን ሃሳብ የማጫውትህ
የእኔ ማረፍያ ወዳጄ እንተ ነህ
ይኸው በዘመኔ ይህንን አየሁ
እንዳተ የሚሆን አንዳችም አጣሁ
ይኸው በዘመኔ ይህንን አየሁ
እንዳተ የሚሆን አንዳችም አጣሁ
አዝማች · Chorus
ማን ይተካል ታዲያ በአንተ ቦታ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኢየሱስ ብቻ ነህ ለእኔ ጌታ
ለማንም አልሰጥም የአንተን ቦታ
ኢየሱስ ብቻ ነህ የእኔ ጌታ
ቁጥር 4 · Verse 4
አዳኝነትህ ተመችቶኛል
በቀን በሌሊት ልቤ ያስብሃል
አትሰለችም ሁሌ ባወራህ
ልቤም ስለዚህ አንተን ፈለገህ
አትሰለችም ሁሌ ባወራህ
ልቤም ስለዚህ አንተን ፈለገህ
አዝማች · Chorus
ማን ይተካል ታዲያ በአንተ ቦታ
ቁጥር 5 · Verse 5
ኢየሱስ ብቻ ነህ ለኔ ጌታ
ለማንም አልሰጥም የአንተን ቦታ
ኢየሱስ ብቻ ነህ የእኔ ጌታ
ቁጥር 6 · Verse 6
ከሃዘኔ ስታጽናናኝ
መከራዬንም ስታስረሳኝ
የልቤ ደስታ አንተ ስትሆን
ይህን አይቼ ወደድኩህ አንተን
የልቤ ደስታ አንተ ስትሆን
ይህን አይቼ ወደድኩህ አንተን
አዝማች · Chorus
ማን ይተካል ታዲያ በአንተ ቦታ
ቁጥር 7 · Verse 7
ኢየሱስ ብቻ ነህ ለኔ ጌታ
ለማንም አልሰጥም የአንተን ቦታ
ኢየሱስ ብቻ ነህ የእኔ ጌታ
ቁጥር 8 · Verse 8
ልቤ እንደ ድንግል ይወድሃል
አንተን ሲያስብህ ደስ ይለዋል
የእኔ ሙሽራ ኢየሱስ ጌታዬ
ፊትህን ሳይ ነው ፍጹ ደስታዬ
የእኔ ሙሽራ ኢየሱስ ጌታዬ
ፊትህን ሳይ ነው ፍፁም ደስታዬ
አዝማች · Chorus
ማን ይተካል ታዲያ በአንተ ቦታ
ቁጥር 9 · Verse 9
ኢየሱስ ብቻ ነህ ለኔ ጌታ
ለማንም አልሰጥም የአንተን ቦታ
ኢየሱስ ብቻ ነህ የእኔ ጌታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ