Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አማራጭ የለም

Amarach Yelem

2007 · ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኢየሱስ እውነት ሕይወት ነው

ኢየሱስ አማራጭ የለው

በእርሱ መዳን በእርሱ ነው በሉ (፪x)

ጌታን የማያውቅ በጨለማ ይኖራል

በምድርም ሲኖር ተደናብሮ ያልፋል

የዓለም ዝብርቅርቅ ጊዜያዊ እኮ ነው

የዘለዓለም ሕይወት ያለው በኢየሱስ ብቻ

ኢየሱስ እውነት ሕይወት ነው

ኢየሱስ አማራጭ የለው

በእርሱ መዳን በእርሱ ነው በሉ (፪x)

የፈጠረህማ እጅጉን ቢወድህ

አንድያ ልጁን በነጻ እንዲሁ ሰጠህ

አንድ ልጁን ሰጠህ

ምክንያትን አታብዛ ሰበብህን አቁም

ይልቅ ልቦናህን ወደ አምላክም መልስ

ኢየሱስ እውነት ሕይወት ነው

ኢየሱስ አማራጭ የለው

በእርሱ መዳን በእርሱ ነው በሉ (፪x)

ነገ ዛሬ አትበል ነገ የአንተ አይደለም

የመዳኛ ሰዓት ቢኖር አሁኑኑ ነው

ሰዓቱ አሁን ነው

አምልጠኸው ውጣ ያሰረህ ጠላት ነው

ትብታብህ ይፈታል ኢየሱስን ጌታህ ስታደርገው

ኢየሱስ እውነት ሕይወት ነው

ኢየሱስ አማራጭ የለው

በእርሱ መዳን በእርሱ ነው በሉ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ