ሃሌ ሃሌሉያ
Hale Hallelujah
2007 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አዝ፣ ሃሌ ሃሌሉያ
ማለት ነው የሚያረካኝ
እኔ ከዚህ በላይ
ሌላ ቃል አይበቃኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታዬ ወዳጄ
ልልህ እወዳለሁ ባለችኝ ቋንቋዬ (አቅሜ)
ዓለም ሳይፈጠር ተመስግኖ ኖሯል
ዓለምም ተፈጥሮ እስካሁን ተመልኳል
ትልቁም ትንሹም ገናና ብሎታል
እኔም ደግሞ አሁን ያንኑ ልደጋግም
አዝማች · Chorus
አዝ፣ ሃሌ ሃሌሉያ
ማለት ነው የሚያረካኝ
እኔ ከዚህ በላይ
ሌላ ቃል አይበቃኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍልስፍና በዝቶ ዕውቀት ተከማችቶ
ጥበብ በጥበብ ላይ ሲታይ ተደርቦ
ቆም ብዬ አሰብኩት የፈጠረውን
ሁሉንም አዋቁ ብልህ መሆኑን
አዝማች · Chorus
አዝ፣ ሃሌ ሃሌሉያ
ማለት ነው የሚያረካኝ
እኔ ከዚህ በላይ
ሌላ ቃል አይበቃኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሊቅ ዕውቀት ቀርቶ የረቀቀውን
መቼ ቀላል ሆነ የሰውስ ጥበብ?
ሁሉን ለፈጠረ ለዚህ ድንቅ ጌታ
ሃሌሉያ እንጂ ምን ሊባል ነው ታዲያ?
አዝማች · Chorus
አዝ፣ ሃሌ ሃሌሉያ
ማለት ነው የሚያረካኝ
እኔ ከዚህ በላይ
ሌላ ቃል አይበቃኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ