አንተ ገናና
Ante Genana
2007 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተ ገናና ሆይ ሁሉን ትገዛለህ
አንተ ገናና ሆይ ሁሉን ትችላለህ
ችሎታህ ሳይለወጥ (፫x)
አቅምህም ሳይለወጥ (፫x)
ሁሉንም ታስተዳድራለህ
በፀጋህ ታስተዳድራለህ (፪x)
አመሰግንሃለሁ አመሰግንሃለሁ
አመሰግንሃለሁ አመሰግንሃለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከፊቴ ስትቀድምልኝ እጄን ይዘህ ስታወጣኝ
ያለፈውን ክፉ ዘመን አሳልፈህ ስታስቀኝ
ታዲያ እንደዚህ አድርገህላኝ
እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ
ተነስቼ ለአንተ ጌታ ምሥጋናዬን አቀርባለሁ
እንዴት ዝም እላለሁ እንደዚህ አድርገህልኝ
እንዴት ዝም እላለሁ ፀሎቴን ሰምተህልኝ
እንዴት ዝም እላለሁ ጠላቴን አባረህልኝ
እንዴት ዝም እላለሁ ሸለቆዬን ሞልተህልኝ
አዝማች · Chorus
አንተ ገናና ሆይ ሁሉን ትገዛለህ
አንተ ገናና ሆይ ሁሉን ትችላለህ
ችሎታህ ሳይለወጥ (፫x)
አቅምህም ሳይለወጥ (፫x)
ሁሉንም ታስተዳድራለህ
በፀጋህ ታስተዳድራለህ (፪x)
አመሰግንሃለሁ አመሰግንሃለሁ
አመሰግንሃለሁ አመሰግንሃለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰምተህ ዝም ማለት አታውቅም
ፀሎቴን አትንቅም
መቼ ሆኖልህ የእኔ ነገር
አቤት ጉድ ነው የአንተስ ፍቅር
ታዲያ እንደዚህ አድርገህልኝ
እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ
ተነስቼ ለአንተ ጌታ ምሥጋናዬን አቀርባለሁ
እንዴት ዝም እላለሁ
አዝማች · Chorus
አንተ ገናና ሆይ ሁሉን ትገዛለህ
አንተ ገናና ሆይ ሁሉን ትችላለህ
ችሎታህ ሳይለወጥ (፫x)
አቅምህም ሳይለወጥ (፫x)
ሁሉንም ታስተዳድራለህ
በፀጋህ ታስተዳድራለህ (፪x)
አመሰግንሃለሁ አመሰግንሃለሁ
አመሰግንሃለሁ አመሰግንሃለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ