ዋናዬ ኢየሱስ
Wanayie Eyesus
2007 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
፣ኢየሱስ ዋናዬ ነህ ኢየሱስ (፪x)
እኔ የማመልከው አንድ ነው
ስሙም ኢየሱስ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አልችልበትም ለሌላ መስገድ
እኔ ማመልከው አንድ ነው
ስሙም ኢየሱስ (፪x)
አንድ ሁለት ብል ሶስተኛ አራተኛ
ኢየሱስ የሕይወቴ ምዕራፍ መጀመሪያ
እረፍቴ ሰላሙ ቤቴን ሞላ
ቃል ገባሁኝ ላላመልክ ከሱ ሌላ
መውደዱ ቤቴ አቆመኝ ፍቅሩ ሁሉን አስጣለኝ (፪x)
የልቤ ማረፊያ ዋናዬ እርሱ ነው (፬x)
አዝማች · Chorus
፣ኢየሱስ ዋናዬ ነህ ኢየሱስ (፪x)
እኔ የማመልከው አንድ ነው
ስሙም ኢየሱስ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እጆቼን አንስቼ ተማረክሁለት
ጠቅልሎ ሊገዛው የእኔን ማንነት
ሁሉ ይቅር ምንም ከሱ አይበልጥም
መሻቴ ይኸ ነው ጌታን ማስቀደም
መውደዱ ቤቱ አቆመኝ ፍቅሩ ሁሉን አስጣለዝኝ
የልቤ ማረፊያ ዋናዬ እርሱ ነው
አዝማች · Chorus
፣ኢየሱስ ዋናዬ ነህ ኢየሱስ (፪x)
እኔ የማመልከው አንድ ነው
ስሙም ኢየሱስ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ