በአምላኬ
Bamlakie
2007 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በአምላኬ ደስ አለኝ
በፍቅሩ ረካሁኝ (፪x)
ሕዝብህን ለማዳን ፈጥነህ ትነሣለህ
የተቀባውንም ትታደገዋለህ
እኔስ መጠጋቴ አንተኑ ላምን ነው
መፎከሪያዬ ነህ የሚነካኝ ማነው (፫x)
አዝማች · Chorus
ማነው ጌታ እንዳንተ ማነው
ማነው እንዳንተ የሚወደው
ማነው ኧረ እርሱ ማነው (፪x)
አቤቱ እንዳንተ የሚሆን
አቤቱ እንዳንተ የሚደርስ
አቤቱ እንዳንተ የሚወድ
አቤቱ እንዳንተ የሚራራ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ የሠራኸው ለእኔ ተቆጠረ
ይኸ ደግሞ ሳያንስ ስሜ ተቀየረ
ልሳቅ እንጂ በደንብ በከሳሼ ላይ
መርገም ተሰበረ ኢየሱስን ሳይ
መርገም ተሰበረ መድኃኒቱን ሳይ
መርገም ተሰበረ ኢየሱስን ሳይ
አዝማች · Chorus
ማነው ጌታ እንዳንተ ማነው
ማነው እንዳንተ የሚወደው
ማነው ኧረ እርሱ ማነው (፪x)
አቤቱ እንዳንተ የሚሆን
አቤቱ እንዳንተ የሚደርስ
አቤቱ እንዳንተ የሚወድ
አቤቱ እንዳንተ የሚራራ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የጠላቴን ራስ አስረግጠኸኛል
ድልን እያበዛህ አስደንቀኸኛል
ኩራት ኩራት አለኝ የእኔ እንደሆንክ ሳስብ
ፍጥረት ሁሉ ይወቅ አምላኬ መሆንህን (፫x)
ማነው ጌታ እንዳንተ ማነው
ማነው እንዳንተ የሚወደው
ማነው ኧረ እርሱ ማነው (፪x)
በአምላኬ ደስ አለኝ
በፍቅሩ ረካሁኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ