አምንሃለሁ
Amnehalehu
ትራክ 8 · 4:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በመልካሙ ቃልህ ልቤን ምታቀና
ታማኙ ወድጄ ይድርስህ ምሥጋና
እግሮቼን ለጥፋት አትተዋቸውም
ጠባቂዬን አንተን አልጠራጥርም
አዝማች · Chorus
አምንሃለሁ አንተን አምንሃለሁ
አምንሃለሁ ጌታ አምንሃለሁ
አምንሃለሁ ጌታ ነፍሴን ሰጥሃለሁ
ሰላም ዓለኝ በአንተ ከሥጋት አርፋለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ታማኝ ነው እጅህ ይዞኛል ላይለቀኝ
ለኔ የተመቸኝ እጅህ ነው የደላኝ
የልመናዬን ቃል የምሰማልኝ
ተስፋ እንደምትሰጠኝ የምትፈጽምልኝ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ብቻ ነህ የልቤ ጋደኛ
ክፋት የሌለብህ ሁሌ እውነተኛ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ