ኢየሱስ አንተ ነህ
Eyesus Ante Neh
ትራክ 1 · 6:27 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ አንተ ነህ ኢየሱስ አንተ ነህ
ኢየሱስ አንተ ነህ እኔ ደስ ያሰኘህ
ኢየሱስ አንተ ነህ ኢየሱስ አንተ ነህ
ኢየሱስ አንተ ነህ እኔ ደስ ያሰኘህ
ቁጥር 1 · Verse 1
አድነኸኛል ከሞት
መጥተህ ወዳላሁበት
ከዚህ የተነሳ አረፍኩኝ
ይኸው ምሥጋንና አመጣሁኝ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለማዳንህ ምሥጋና ይኸው
ምሥጋና ለማዳንህ ምሥጋና
ተባረክ ጌታዬ ተባረክ ኦሆ
ተባረክ አምላኬ ተባረክ
ቁጥር 2 · Verse 2
ተጨንቀኽልኝ ስለኔ
ሰላምን ሰጠኸኝ ለኔ
እንደ ወንዝ በልቤ ፈሳል
ይኸው ምሥጋናዬን ተቀበል
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለሰላምህ ምሥጋና ይኸው
ምሥጋና ለሰላምህ ምሥጋና
ተባረክ ጌታዬ ተባረክ ኦሆ
ተባረክ አምላኬ ተባረክ
ቁጥር 3 · Verse 3
በልቅሶ በሃዘን ፈንታ
አስታጥቀኸኛል ደስታ
መከራን በአንተ ረስቼ
ይኸው ምጋናህን አብዘቼ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለደስታህ ምሥጋና ይኸው
ምሥጋና ለደስታህ ምሥጋና
ተባረክ ጌታዬ ተባረክ ኦሆ
ተባረክ አምላኬ ተባረክ
ቁጥር 4 · Verse 4
ምንም አያሻኝ ረክቼ
ጌታን አንተን ተጠግቼ
ጌታ በልቤ ከብረሃል
አፌም ምግናህን ያወራል
በዚህች ዕውቀት እንዲህ ካረካኸኝ
ብዙ ባውቅህ ምን እሆናለሁኝ
ናፍቃለሁ ጌታ ብዙ ላውቅህ
ብዙ ብዙ ስግደት ላመጣልህ
በቀረው ዘመኔ ውርስ የምፈልገው
ብር ወርቅን አይደለም ጌታዬ አንተን ነው
ዛሬ ያለኸን አንተ ምሻውም አንተን ነው
ነገም ከዛ ወዲያ መሻቴ አንተን ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ