ምሥጋናዬ ለአንተ
Mesganayie Lante
ትራክ 9 · 4:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በፊትህ መሆን ነው ደስታዬ
ድምጽህ ጣፋጭ ሆናል ለጆሮዬ
ከአንተ ሌላ የለም የሚያረካኝ
እንተ ነህ እግዚአብሔር ምተመችኝ
አዝማች · Chorus
እንተ ነህ እግዚአብሔር ምተመችኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ምሥጋናዬ ለአንተ ለጌታዬ
አምልኮዬ ለአንተ ለጌታዬ
ዝማሬዬ ለአንተ ለጌታዬ
አመልክሃለሁኝ በምሥጋና
አዜምልሃለሁ በምሥጋና
አቀኝልሃለሁ በምሥጋና
አንተን እንጂ ምንም አልፈልግም
እንዳንተ የሚሆን ማንም የለም
ለኔ እግዚአብሔር ወዳጄ ነህ
በዚህ ደስ አለኝ ላመስግንህ
አዝማች · Chorus
በዚህ ደስ አለኝ ላመስግንህ
ቁጥር 3 · Verse 3
የሚጠቅመኝ የለም በዚህች ምድር
ከአንተ በስተቅር ከእግዚአብሔር
አስፍቼ እሄዳለሁ በመንገድህ
ተድላ ሆኖልኛል ትህዛዝህ
ሰላም ሆኖልኛል ትህዛዝህ
ነፍሴ ዝም ብለሽ አመስግኚው
እግዚአብሔር አምላክሽን እርሱን ወደጂው
ልጅን በመሰዋት አቅርቦሻል
በፍቅሩ ሁልግዜ ያረካሻል
አዝማች · Chorus
በፍቅሩ ሁልግዜ ያረካሻል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ