እሰይ አባት አለን በሰማይ
Esey Abat Alen Besemay
ትራክ 5 · 3:17 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እሰይ እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ እሰይ
አባት አለን በሰማይ
ቁጥር 1 · Verse 1
ወፎች ሚመግባቸው
አበቦችን ያሳመራቸው
ከእነርሱ አስበልጦናል
አባታችን ያስብልናል
ጠላቶች ሳለን የወደደን
በውድ ልጁ የታረቀን
ስንለምነው ይሰማናል
መንፈሱን ያፈስልናል
እኛ ክፉዎች ስንሆን
ልጆቻንን ከወደድን
እርሱ የሰማይ አባታችን
ደግ ነው የሚያስብልን
እጅግ የሚምር የሚራራ
አባት አለ ከእኛ ጋራ
እርሱ ነው የእኛ አባታችን
ሚያስብ ሚጠነቀቅልን
አዝማች · Chorus
እሰይ እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ እሰይ
አባት አለን በሰማይ
ቁጥር 2 · Verse 2
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
በሰማይ አባት አለን
ቁጥር 3 · Verse 3
አባ አባ እንድንለው
መንፈሱን በእኛ አፈሰሰው
ልጆቹ አድርጐናል
አባት አለን ያስብልናል
ፍጻሜና ተስፋ ሰጭያችን
እርሱ የሰላም አምላካችን
እግዚአብሔር ይወዳናል
ክማንም ይልቅ ቀርቦናል
አዝማች · Chorus
እሰይ እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ እሰይ
አባት አለን በሰማይ
ቁጥር 4 · Verse 4
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
በሰማይ አባት አለን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ