Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኦ ምሥጋና

O Mesgana

ትራክ 7 · 3:29 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኦ ምሥጋና ለጌታ ኦ ምሥጋና ለኢየሱስ

ኦ ምሥጋና አሜን ለአምላኬ ይገባዋልና (፪x)

ጠላት ዙሪዬን ሲከበኝ

ወደ አምላኬ አነባሁኝ

መብረቁን ከሰማይ ላከ

የሚያውከኝን አወክ

የሚገፋኝን እየገፋ

ጌታ ድንበሬን አሰፋ

ያስጨነቀኝ እስጨነቀ

ስሙን በኔ ላይ አደመቀ

ጠላት በቃሉ ሲያደናግረኝ

ከያዝኩት እውነት ሊያላቅቀኝ

አምላኬ አይቶ ሳቀበት

መታሰቢያውን ሁሉ አጠፋበት

ግራ ያጋባኝ ተበተነ

እንደ ገላባ በነነ

ወጥመድ መንገዴን ዘርግቶበት

በላዩ ወድቆ ተያዘበት

የክፉውን ውሸት ገለበጠ

የእግዚአብሔር እውነት ተገለጠ

በቤቴ ሰላም እረፍት ሆነ

የሱስ በኑሮዬ ገነነ

የሱስ በልቤ ስፍራ ያዘ

ንፋሱ ፀጥ አለ ታዘዘ

ማህበል ወጀቡን ገሰፀው

መርከቡን በሰላም አስኬደው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ