Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንበሳው

Anbesaw

2008 · ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከሁሉም የሚበልጥብኝ በማንም የማለውጠው

አንበሳው የጀግኖች ጀግና ኢየሱስ መድሃኒቴ ነው (፪x)

ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ ነው

ፍቅሩ ግሩም እጁ ሰፊ ነው

ምንተስኖት ምን ያሳጣኛል

ቸርነቱን አብዝቶልኛል (፪x)

ያለፈው ታሪኬ አፍ አለው ያወራል

የጌታን ምህረት ፍቅር ይዘክራል

ያልተደረገልኝ ያልሆነ ምን አለ

የአምላኬ ምህረት በእኔ ገነነ

ያልተደረገልኝ ያልሆነ ምን አለ

የጌታ ምህረት በእኔ ገነነ

ይረዳል እኮ ከማንም በላይ

ተገርሜያለሁ ተአምራቱን ሳይ

ምስክሩ ነኝ ሕያው ምልክቱ

ማዳኑን ያየሁ ሁሉን ቻይነቱን (፪x)

ከሁሉም የሚበልጥብኝ በማንም የማለውጠው

አንበሳው የጀግኖች ጀግና ኢየሱስ መድሃኒቴ ነው (፪x)

ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ ነው

ፍቅሩ ግሩም እጁ ሰፊ ነው

ምንተስኖት ምን ያሳጣኛል

ቸርነቱን አብዝቶልኛል (፪x)

ምህረቱን እውነቱን ፍቅሩን አስብና

የከበረ ስሙን አሞጋግስና

ሳመልከው ሳከብረው እጅግ ደስ ይለኛል

እንደ ኢየሱስ/ጌታ ከየት ይገኛል (፪x)

ልዘምር ድንቁን በምክሩ ስቦኛል

አምላክ ለክብሩ በስሜ ጠርቶኛል

ያስደስተኛል የጌታ መሆኔ

ምህረት አገኘሁ ዳንኩኝ ከኩነኔ (፪x)

ከሁሉም የሚበልጥብኝ በማንም የማለውጠው

አንበሳው የጀግኖች ጀግና ኢየሱስ መድሃኒቴ ነው (፪x)

ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ ነው

ፍቅሩ ግሩም እጁ ሰፊ ነው

ምንተስኖት ምን ያሳጣኛል

ቸርነቱን አብዝቶልኛል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ