የተመሰገነ
Yetemesegene
2008 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በሰማይ በምድር የተመሰገነ
በስራው ጻድቅ ነው እጅግ የታመነ
ሰማይን በኃይሉ በቃሉ ያጸና
እግዚአብሔር ታላቅ ነው ገናና
ኦሆ ገናና ነው (፪x)
እግዚአብሔር ታላቅ ገናና ነው
ኦሆ ገናና ነው (፪x)
የእኛ ጌታ ታላቅ ገናና ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
እናንተ መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ
ንጉሡን ንጉሡን አስገቡ
ይህ የክብር ንጉሥ ግርማው የሚያስፈራ
በኃይሉ ተዐምር የሚሰራ
ሃያል ሃያል እርሱ ነው ብርቱና ሃያል (፫x)
ሃያል ሃያል ኢየሱስ ነው ብርቱና ሃያል
አዝማች · Chorus
በሰማይ በምድር የተመሰገነ
በስራው ጻድቅ ነው እጅግ የታመነ
ሰማይን በኃይሉ በቃሉ ያጸና
እግዚአብሔር ታላቅ ነው ገናና
ኦሆ ገናና ነው (፪x)
እግዚአብሔር ታላቅ ገናና ነው
ኦሆ ገናና ነው (፪x)
የእኛ ጌታ ታላቅ ገናና ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር ብርቱ በሰልፍም ሃይለኛ
ተዋጊ ለተጠቃው ዳኛ
የዙፋኑ መሰረት ጽድቅና እውነት ነው
እልልታ ክብር ለሚገባው
ሰማይ ዙፋኑ ነው ምድር የእግሩ መርገጫ
በታሪክ ነው የሌለው አቻ
እግዚአብሔር አምላክ ነው በማን ይመሰላል
በግርማው ፍጥረት ይደነቃል
ሃያል ሃያል እርሱ ነው ብርቱና ሃያል
ሃያል ሃያል ጌታ ነው ብርቱና ሃያል (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይ በምድር የተመሰገነ
በስራው ጻድቅ ነው እጅግ የታመነ
ሰማይን በኃይሉ በቃሉ ያጸና
እግዚአብሔር ታላቅ ነው ገናና
ኦሆ ገናና ነው (፪x)
እግዚአብሔር ታላቅ ገናና ነው
ኦሆ ገናና ነው (፪x)
የእኛ ጌታ ታላቅ ገናና ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ኦሆ ገናና ነው (፪x)
እግዚአብሔር ታላቅ ገናና ነው
ኦሆ ገናና ነው (፪x)
የእኛ ጌታ ታላቅ ገናና ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ