ይጠብቀኛል
Yetebeqegnal
2008 · ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በቀንም በሌሊት ጌታዬ ይጠብቀኛል
አሃአሃ ይጠብቀኛል እህእህ
እንደ አምላኬ ያለ ከወዴት ይገኛል
አሃአሃ ከየት ይገኛል ሆሆሆ ከየት ይገኛል
ቁጥር 1 · Verse 1
መውጣቴ መግባቴ ከእርሱ ተጠብቆ
ባለፍኩበት መንገድ ጌታ ለእኔ ተተንቅቆ
በምህረቱ ታድጓታል ነፍሴን ከእሳት ነጥቆ
የእርሱን ደግነት ለሰው እነግራለው
አያሳፍርም ሁሌ ታማኝ ነው
በሥም የሚያውቀኝ የሆነኝ ጥላ
ኢየሱስ እኮ ነው የኔ ከለላ
አዝማች · Chorus
በቀንም በሌሊት ጌታዬ ይጠብቀኛል
አሃአሃ ይጠብቀኛል እህእህ
እንደ አምላኬ ያለ ከወዴት ይገኛል
አሃአሃ ከየት ይገኛል ሆሆሆ ከየት ይገኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
ትንፋሼን መንገዴን በእጁ ለያዘው
የሰማዩን ፍቅር ሰላም ውስጤ ላፈሰሰው
በማዳኑ ደስ እያለኝ አመሰግናለሁ
ታሪክም የለኝ ታሪኬ እርሱ ነው
ከልጅነቴ እጄን የያዘው
ምስክሩ ነኝ ዘለዓለም ይንገሥ
መልካም እረኛ ስሙ ኢየሱስ
አዝማች · Chorus
በቀንም በሌሊት ጌታዬ ይጠብቀኛል
አሃአሃ ይጠብቀኛል እህእህ
እንደ አምላኬ ያለ ከወዴት ይገኛል
አሃአሃ ከየት ይገኛል ሆሆሆ ከየት ይገኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ