ፍጥረት የሚደገፍበት
Fetret Yemidegefebet
2008 · ትራክ 12 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ፍጥረት የሚደገፍበት
እኔም ተስፋ ማደርግበት
ጌታ ነው እንከን የሌለበት
ልዘምር እስቲ ልቀኝለት
ለሕይወት ጥያቂ ለእንቆቅልሹ
ጌታ ነው ምላሽ አቻ የለሹ
ሁሉንም መልካም ያደርገውና
ያስገርመናል ድንቅ ይሰራና
ያድንና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ይባርክና (ኦሆሆሆሆ)
ሰው ያደርግና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ያቆምና (ኦሆሆሆሆ)
ይደግፍና
ቁጥር 1 · Verse 1
እየባረኩኝ እባርክሃለሁ
በሕይወትህ ድንቅን አደርጋለሁ
ከአንተ ጋር ነኝ አትፍራ እንዳልከኝ
የኔ ጌታ ስንቱን አሳለፍከኝ
ስንት ጊዜ አዳንከኝ ከጥፋት
ልገልጽ አልችል የውለታህን ብዛት
ድንቅን አይቻለሁ ድንቅን አይቻለሁ
በሕይወት ዘመኔ ገና አመልክሃለሁ
ድንቅን አይቻለሁ ድንቅን አይቻለሁ
በሕይወት ዘመኔ እገዛልሃለሁ
አዝማች · Chorus
ፍጥረት የሚደገፍበት
እኔም ተስፋ ማደርግበት
ጌታ ነው እንከን የሌለበት
ልዘምር እስቲ ልቀኝለት
ለሕይወት ጥያቂ ለእንቆቅልሹ
ጌታ ነው ምላሽ አቻ የለሹ
ሁሉንም መልካም ያደርገውና
ያስገርመናል ድንቅ ይሰራና
ያድንና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ይባርክና (ኦሆሆሆሆ)
ሰው ያደርግና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ያቆምና (ኦሆሆሆሆ)
ይደግፍና
ቁጥር 2 · Verse 2
ቁሻሻውን ታሪኬን ለውጠህ
ሰው አደረከኝ ኢየሱስ በእኔ ከብረህ
ገና ህጻን ሳለሁ የተሸከምከኝ
በጉያህ ውስጥ እስካሁን አለሁኝ
አልተውህም አልጥልህም ያልከኝ
ኢየሱሴ ከፍ ከፍ በልልኝ
ድንቅን አይቻለሁ ድንቅን አይቻለሁ
በሕይወት ዘመኔ ገና አመልክሃለሁ
ድንቅን አይቻለሁ ድንቅን አይቻለሁ
በሕይወት ዘመኔ እገዛልሃለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ