በአንተ ደስ ይለኛል
Beante Des Yelegnal
2008 · ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አሁንማ ፤ ብርሃንህ በእኔ ደምቋል
መከራም ከኔ ርቋል በአንተ ደስ ይለኛል
ምን እላለሁ ፤ ስምክን ከማክበር በቀር
ምን ልበል ምን ልናገር ስላደረክልኝ ነገር (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በዓለም ላይ ከሚታየው ከአልማዝ ከወርቅ ከዕንቁ
የአንተ ፍቅር ይበልጣል አባት ነህ ለተጠቁ
ምስክር ነኝ ለዚህ እኔ ማዳንህን አይቻለሁ
ያባትነት ፍቅርህን ምህረትህን እዘምራለሁ
ተመስገን እያልኩ ላክብር ስምህን
በእርግጥ ስላየሁ ጌትነትህን
በአማረ ዜማ ቅኔ ውዳሴ
ልዑል ከፍ በል ያክብርህ ነፍሴ
አዝማች · Chorus
አሁንማ ፤ ብርሃንህ በእኔ ደምቋል
መከራም ከኔ ርቋል በአንተ ደስ ይለኛል
ምን እላለሁ ፤ ስምክን ከማክበር በቀር
ምን ልበል ምን ልናገር ስላደረክልኝ ነገር (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ማረፊያ ለምስኪኑ ማጠጊያ ለደሃው ሰው
ይህንን አይቻለሁ እንባውን ስታብሰው
ደግ ነህ እግዚአብሔር መልካም ግሩም በምክርህ
ምህረትህ አይለካም ወደር የለው ለፍቅርህ
አሉ ብዙዎች የታደጋቸው
ስምህን የሚጠሩ በምሥጋናቸው
እያደነቁ ግሩም ስምህን
ይዘምራሉ ጌትነትህን
አዝማች · Chorus
አሁንማ ፤ ብርሃንህ በእኔ ደምቋል
መከራም ከኔ ርቋል በአንተ ደስ ይለኛል
ምን እላለሁ ፤ ስምክን ከማክበር በቀር
ምን ልበል ምን ልናገር ስላደረክልኝ ነገር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ