Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኢየሱስ

Eyesus

2008 · ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያ የጥንቱ ፍቅራችን መሃላችን የታለ

ኀጢአታችን በዝቶ ጥላቻን አበቀለ

ከአንተ ያልተቀበልነው ያልሰጠኸን ምን አለ

ሁሉም ተረስቶ ዛሬ ትዕቢታችን ከፍ አለ

ኢየሱስ (፪x) በማስተዋል ሙላን በማስተዋል (፪x)

ኀጢአት ከንቱ ነው አይሆንም ልማት

ሞትን ይወልዳል ለሕይወት ጥፋት

ደሙ ያላጠበው ያልተመለሰ

እናስብ እንጂ ከየት ደረሰ

ምክንያት አንደርድር ለድካማችን

ከሞት ያድናል መመለሳችን

ኑሯችን ከንቱ ከእውነት የሚጣረስ

ንሰሃ እንግባ ሳናለባብስ

ቦታ አጥቶ ቅድስና ኀጢአት ተሞልቷል ቤቱ

ሁሉም አንተን አልፈራም ይስታል በአንደበቱ

የጥበብ መጀመሪያው አንተን መፍራቱ ጠፍቶ

ሁሉ እንዳሻው ይሄዳል ቤቱ በአመጽ ተሞልቶ

ኢየሱስ (፪x) በማስተዋል ሙላን በማስተዋል (፪x)

ከየት ተማርነው ወንድምን መጥላት

ከነብያት ነው ወይንስ ከሓዋርያት

የቀደሙትን የምናውቃቸው በመልካም ፍቅር በጸሎታቸው

ለእውነት እንኑር ከቶ አንገበዝ

ደሙ ያነጻናል ቶሎ እንመለስ

የሰማይ ጥበብ የላይኛይቱን

ከአምላክ እንለምን ይሰማል ሁሉን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ