Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክበርልኝ

Keberelegn

2008 · ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የድሃን ማድጋ ዘይት የሚሞላው

ከችግር አውጥቶ በደስታ ሚያኖረው

ለአንድ አይደለም ኢየሱስ ለብዙ ይተርፋል

ክበር እንበለው ይገባዋል

ክበር ክበርልን ክበር እንበለው

መክበር የሚገባው ቸር አምላክ ነው

ለቅሶን ወደ ደስታ ወደ ሳቅ ለውጧል

ኢየሱስ ሊመሰገን ይገባዋል

በሽባነት ታስሮ እንድሜውን ለፈጀው

ወዳጅ ዘመድ ትቶት ተስፋ ለቆረጠው

ታምረኛው ኢየሱስ በጊዜው ይደርሳል

እስራቱን ፈቶ ያዘልላል

ክበር ክበርልን ክበር እንበለው

መክበር የሚገባው ቸር አምላክ ነው

ለቅሶን ወደ ደስታ ወደ ሳቅ ለውጧል

ኢየሱስ ሊመሰገን ይገባዋል

ሙቱን ከመቃብር ተጣርቶ ያስነሳል

በቃ የተባለውን ነፍስ ይዘራበታል

ለእርሱ ማይታዘዝ ምን አለ በውኑ

ከፍ ብሎ ይንገሥ በዙፋኑ

ክበር ክበርልን ክበር እንበለው

መክበር የሚገባው ቸር አምላክ ነው

ለቅሶን ወደ ደስታ ወደ ሳቅ ለውጧል

ኢየሱስ ሊመሰገን ይገባዋል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ