አንድን ነገር
Anden Neger
2003 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔርን አንድን ነገር ለምኜዋለሁ
ያንን ከእጁ እናፍቃለሁ
ቁጥር 1 · Verse 1
አሮጌውን በአዲስ ተክቶ
እስኪወስደኝ ጌታዬ መጥቶ
የሞተልኝ ወዳጄን እስካይ
ናፍቆቴ እስኪፈጸም በሰማይ
እንዲጠብቀኝ ምድር ላይ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔርን አንድን ነገር ለምኜዋለሁ
ያንን ከእጁ እናፍቃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
በሕይወቴ ዘመን በሙሉ
ልኖር እኔም እንደ ሕያው ቃሉ
ምኞቴ ነው ይህ አንድ ነገር
እስካለሁ በዚህች ጠፊ ምድር
ይህን ነገር እናፍቃለሁ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔርን አንድን ነገር ለምኜዋለሁ
ያንን ከእጁ እናፍቃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
የመምጫህን ቀን ስለማላውቅ
ጌታ ኢየሱስ የአንተን መገለጥ
ያለ ነውርና ነቀፋ
ሆኜ እንድጠብቀው በተስፋ
ይህን ነገር እናፍቃለሁ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔርን አንድን ነገር ለምኜዋለሁ
ያንን ከእጁ እናፍቃለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ