ልዩ ነህ
Leyu Neh
2003 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተ እኮ ለእኔ ጌታ ነህ
አንተ እኮ ለእኔ ልዩ ነህ
አንተ እኮ ለእኔ ወዳጄ ነህ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሥሜን በሰማዩ መዝገብ መቀመጫዬን በአብ ቀኝ
እረፍትን ለዘለዓለም ለዘመኔም ቁጥር የለም
ስሄድ በመላዕክት ታጅቤ እኔም በአምላኬ ታስቤ
ሰማያት ደስ እያላቸው እኔ መዳኔ ገርሟቸው
በትውልድ ላላገኘሁት
በትምህርት በዕውቀት በችሎታ
የማያልፍ ክብር አውራሼ
አዝማች · Chorus
ልዩ ነህ ለእኔ የእኔ ጌታ
ልዩ ነህ ጌታ ልዩ ነህ
ልዩ ነህ ኢየሱስ ለእኔስ ልዩ ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለጥበቃህ አልሰጋም ተጠብቄ አይቻለሁ
ስለማዳንህ ብናገር አለኝ ብዙ አወራለሁ
አባትነትህማ ለእኔ ሆኖኝ ጧት ማታ ትዝታ
እኖራለሁ ተደስቼ በአንተ በአስደናቂ ጌታ
በዘመድ አልታመንም
ዛሬ ታይቶ በሚጠወልግ
ብሩንም አይቼዋለሁ
እንደ ጉድፍ ቆጥሬዋለሁ
በምንም የማይገመት ሀብቴ
ትምክህቴ ልዩ ኩራቴ
የሕይወት ዘመን ምርጫዬ
አዝማች · Chorus
አንተ ነህ ለእኔስ ጌታዬ
ማንም ላይገዛኝ ኖራለሁ ሁሉን በአንተ አሸንፌአለሁ
የሚገዛኝ በዚህ ዓለም ከአንተ ውጭ ማንም የለም
ቁጥር 3 · Verse 3
ገንዘብ ሀብት ዕውቀት ንብረት በዚህ ዓለም ነገር መጠመድ
አበቃ አከተመለት ከአንተ የተገናኘን ዕለት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ