ማንንም አይጥልም
Manenem Aytelem
2003 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጠላቴ ሆይ ስማኝ
ዛሬም እነግርሃለሁኝ
ብወድቅ እነሣለሁኝ
በጨለማ ብቀመጥም እንኳን
እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል
እርሱ ወጥመድህን ይቆርጥልኛል
አይምሰልህ ለዘለዓለም
አምላኬ ማንንም አይጥልም
ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም
ቁጥር 1 · Verse 1
በድካሜ የሚራራልኝ የእግዚአብሔር ልጅ ስላለልኝ
ወደ ብርሃን ያወጣል ክብሩን በግልጽ ያሳየኛል
ሁለቴም ባይንሽ ታያለሽ በዕፍረት ትከደኛለሽ
ትረገጭ እንደ ጭቃ ይህ ሊሆን ግድ ነው በቃ
አዝማች · Chorus
ጠላቴ ሆይ ስማኝ
ዛሬም እነግርሃለሁኝ
ብወድቅ እነሣለሁኝ
በጨለማ ብቀመጥም እንኳን
እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል
እርሱ ወጥመድህን ይቆርጥልኛል
አይምሰልህ ለዘለዓለም
አምላኬ ማንንም አይጥልም
ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም
ቁጥር 2 · Verse 2
ሙሴ እናቱ ስትጥለው የምታደርገው ነገር ጠፍቶ
መወሸቂያ መደበቂያ የሚሆን ሥፍራ ለርሱ ታጥቶ
እግዚአብሔር ግን ተቀበለው ከእጇ ሥር ወስዶ አቀፈው
የተፈራ ቤት ሊያኖረው ክብሩን በግል እያሳየው
አዝማች · Chorus
ጠላቴ ሆይ ስማኝ
ዛሬም እነግርሃለሁኝ
ብወድቅ እነሣለሁኝ
በጨለማ ብቀመጥም እንኳን
እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል
እርሱ ወጥመድህን ይቆርጥልኛል
አይምሰልህ ለዘለዓለም
አምላኬ ማንንም አይጥልም
ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም
ቁጥር 3 · Verse 3
መች ይጥላል የእኔ ጌታ?
ያነሣል ወደ ከፍታ
ለጠበቀው ለታገሰው
የሚያኮራ ምላሽ አለው
አዝማች · Chorus
ጠላቴ ሆይ ስማኝ
ዛሬም እነግርሃለሁኝ
ብወድቅ እነሣለሁኝ
በጨለማ ብቀመጥም እንኳን
እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል
እርሱ ወጥመድህን ይቆርጥልኛል
አይምሰልህ ለዘለዓለም
አምላኬ ማንንም አይጥልም
ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ