ከምልህ በላይ ነህ
Kemeleh Belay Neh
2003 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኤልሻዳይ ብዬ ዘምሬአለሁ
ጌታም ነህ ብዬ መስክሬአለሁ
አሁን ግን ቃላትን ስላጣሁ
ከምለው በላይ ነህ ብያለሁ
አዝማች · Chorus
ከምልህ በላይ ጌታ (፫x) ነህ
የእኔ ቃላት የማይገልጽህ የሰው ቃላት
ከምልህ በላይ ጌታ ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔን አሳፍሮኝ አያውቅም የማገለግለው ጌታ
ያኖረኛል በምድር ላይ ጠላቶቼን እየመታ
ለምን ይህን አደረግህ? ብሎ የጠየቀው የለም
ሥልጣኑ ከሁሉ በላይ ጉልበቱ ኤልሻዳይ ነው
አዝማች · Chorus
እሠይ (፮x)
ጌታ ነው በምድር በሰማይ
ከሁሉም በላይ
ነው ኢየሱስ በምድር በሰማይ
ከሁሉም በላይ
ቁጥር 3 · Verse 3
ስለ በደሌ ዝቅ ብሎ መስቀል ተሸክም ያየው ሰው
የሰማይ የምድር ጌታ ነው ብሎ ማን ይገምተው?
ቢሆንም ተነሥቶ ጌታ በዓብ ቀኝ ተቀምጧል
በሰማይና በምድር ሁሉን አንበርክኳል
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ
አይጠቅምም ብለው የጣሉት የትንሣዔ ጌታ ሆነ
የናቁትን አሳፍሮ እጅ አስጭኗቸዋል
በመንግሥቱም እያበራ ዘለዓለም ይኖራል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ