ክብሩ ለአንተ
Kebru Lante
2003 · ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ
ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ
ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ
ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ
ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከዓለም ወጣሁና ምን ይቀርብኛል?
ይመስገን ጌታዬ ሁሉ ሞልቶልኛል
በግርፋት ቁስሉ እርሱ ፈውሷታል
ነፍሴም ከዚህ ውጭ ምን ያስፈልጋታል?
ከዚህ የተሻለ ምን ለውጥ ሊያመጣልኝ
የሚለኝ ጠላቴ ርስትህን ለውጠኝ
አዝማች · Chorus
ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ
ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ
ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ
ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ
ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ራሴን ስመለከት ለዚህ የማልበቃ
እንዴት ተደባለቁ ከአንተ ቅዱስ መንጋ?
ርስትህን አወረስኸኝ ከቅዱሣን ጋራ
ከአንተ ጋር አኖርኸኝ ሰማያዊ ሥፍራ
ምሕረትህ ደርሶኛል ለዚህ በቅቻለሁ
እኔም በዘመኔ እገዛልሃለሁ
አዝማች · Chorus
ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ
ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ
ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ
ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ
ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ታስሬ አግኝተህ ነው አንተ ያስፈታኸኝ
እኔም ነጻ ወጣሁ ጌታ ስላሰብኸኝ
ስለ እኔ የሚጠይቅ አጭር መልስ ያገኛል
ትዕዛዝን ሰጥተህ ነው ብለህ ያስፈልገኛል
ክብርን አለበስኸኝ ውርደቴ ቀረና
ተገረመ ሁሉም መዳኔን አየና
አዝማች · Chorus
ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ
ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ
ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ
ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ
ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
የማመልክህ አምላክ ጊዜያዊ አይደለም
ትላንትና የሌለህ ዓለም የማታውቅህ
አይደለም ጌታዬ ታሪክ ያፈለቀህ
ለዚህች ዓለም እንኳ ራስህ መድኃኒት ነህ
ለጠየቀኝ ሁሉ ለመልስ ዝግጁ ነኝ
ውዴ መድኃኒቴ እኔን እንዳዳንኸኝ
አዝማች · Chorus
ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ
ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ
ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ
ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ
ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ