Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ድንቅ ነህ

Denq Neh

2003 · ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ድንቅ ነህ (፬x) ኢየሱስ ልዩ ነህ

ሃሌሉያ አሃ ሃ

ድንቅ ነህ (፬x)

ለእኔ ክብር ነህ

አስደናቂነትህን አይተን እስከዛሬ

እንጂ መቼ ኖርን? ሰምተን ጭፍን ወሬ

ሥራህን በሕይወታችን ተገልጦ ስላየነው

አናፍርም ያኮራል የአንተ መሆን ክብር ነው

ድንቅ ነህ (፬x) ኢየሱስ ልዩ ነህ

ሃሌሉያ አሃ ሃ

ድንቅ ነህ (፬x)

ለእኔ ክብር ነህ

ቃላት አጣሁ እንጂ ብዙ እናገር ነበር

ጠላት በእኔ ዘግቶ ስለከፈትክልኝ በር

ርስት አገኘሁ እንጂ መች በዚህ አበቃ?

በቤትህ ወግ አየሁ ቀረና ሰቆቃ

ድንቅ ነህ (፬x) ኢየሱስ ልዩ ነህ

ሃሌሉያ አሃ ሃ

ድንቅ ነህ (፬x)

ለእኔ ክብር ነህ

ለእኔ አጋዥ የሚሆን ጠፍቶ ዝም ሲባል

ረዳቴ ሆነኸኝ ከተፍ ብለሃል

የቀራንዮ ወዳጅ ተባረክ ዘለዓለም

የክፉ ቀን ወዳጅ እንዳንተ ያለ የለም

ድንቅ ነህ (፬x) ኢየሱስ ልዩ ነህ

ሃሌሉያ አሃ ሃ

ድንቅ ነህ (፬x)

ለእኔ ክብር ነህ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ