Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅርህ ልዩ ነው

Feqreh Leyu New

2003 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፍቅርህ ልዩ ነው (፬x)

ትላንትን አይቼህ ዛሬም

የማትለወጥ ለዘለዓለም

ኢየሱስን አየሁ የነፍስ ወዳጅ

ፍቅርህ ለዘለዓለምም የማያረጅ

ፍቅርህ ልዩ ነው (፬x)

ይሸከማል እርሱ እስከ ሽበት

አይሰለችም እስከ ሽምግልና

የጠራውን ያውቃል ያጸናዋል

ይመራዋል በክብር ጐዳና

ፍቅርህ ልዩ ነው (፬x)

የማይታለፉትን ቀናት

አለፍኳቸው በአንተ ብርታት

ዛሬ ፀሐይ ወጥቶልኛል

በአንተ ብዙ ሆኖልኛል

ፍቅርህ ልዩ ነው (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ