አንተ እኮ ነህ
Ante Eko Neh
2006 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ወልዶ አይጥልም ጌታ ያሳድጋል
አሳድጎም ለማዕረግ ለወግም ያበቃል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አይቻለሁ በዓይኔ ጌታን በዘመኔ
አይቻለሁ በዓይኔ ጥበቃውን በኔ
አይቻለሁ በዓይኔ ጌታን በዘመኔ
አይቻለሁ በዓይኔ አባት ሆኖኝ ለኔ
አይቻለሁ በዓይኔ ጌታን በዘመኔ
አይቻለሁ በዓይኔ ታማኝ ሆኖ ለኔ
ቁጥር 3 · Verse 3
አስቸጋሪ የሆነውን ዓመሌን ችለሃል
ከማንም ሰው ይልቅ ለኔ አንተ ተመችተኸኛል
አባቴ ሆይ እንዳንተ ያለ ኧረ ማን አለ
በፍቅር የሚያባክን ሁሉንም አይቻለሁ
አዝማች · Chorus
አንተ እኮ ነህ ሰብሳቢዬ ኢየሱስዬ አሳዳጊዬ ኢየሱስዬ (፬x)
መካሪዬ ኢየሱስዬ መጠሪያዬ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ
መካሪዬ ኢየሱስዬ መጠሪያዬ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ያለ አማካሪ ብቻህን ታምራት ታደርጋለህ
ሃጥያተኛን ቀድሰህ ለክብርህ ታቆማለህ
ታሪኬ ታድሶልኝ ይኸው እዘምራለሁ
አዝማች · Chorus
አንተ እኮ ነህ መታሰቢያዬ የሱስዬ መታወቂያዬ ኢየሱስዬ (፬x)
መጀመሪያዬ ኢየሱስዬ መደምደሚያዬ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ
ቁጥር 5 · Verse 5
ጠላት ዙሪያዬን ሲዞር እያገሳ እንደ አንበሳ
ሊውጠኝም ሲከጅል መከራዬን ሲያበዛ
አንተ ተስፋዬ እኮ ነህ ሁሉም በከፋ ጊዜ
ሌላ ረዳት የለኝም ረዳቴ ነህ ኢየሱስዬ
አዝማች · Chorus
አንተ እኮ ነህ ጊዜ ታዳጊዬ ኢየሱስዬ ጠባቂዬ ኢየሱስዬ (፬x)
ማምለጫዬ ኢየሱስዬ መሸሸጊያዬ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ
ቁጥር 6 · Verse 6
ምንም ነገር በሌለበት ምድረበዳ ላይ
ዓይኖቼን በመታመን አንስቼ ወደላይ
ስጠራህ የማትዘገይ ፈጥነህ የምትደርስልኝ
ለችግር ለጭንቀቴ መፍትሔ የምትሆንልኝ
አዝማች · Chorus
አንተ እኮ ነህ (፬x)
መታመኛዬ ኢየሱስዬ መጽናኛዬ ኢየሱስዬ
መመኪያዬ ኢየሱስዬ መኖሪያዬ ኢየሱስዬ አንተኮ ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ