አሻፈረኝ
Ashaferegn
2006 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱስ ሲጠራኝ እርሱን ተከተልኩኝ (፪x)
በጣም ረጅም መንገድ ተጉዤ መጣሁኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከእንግዲህ ወደ ኋላ ዞር ብዬ አላይም
የመጣ ይምጣ እንጂ ከርሱ አልለይም
አሻፈረኝ አሃ ወደኋላ አልመለስም
ወስኛለሁ አንዴ ከኢየሱስ ጋር ነኝ አልለየውም
የረሳሁት ነገር ከኋላ ቢኖርም
ይቅርብኝ ብያለሁ ከኢየሱስ አይበልጥም
ቁጥር 3 · Verse 3
ለእኔ እንደ ኢየሱስ ማን ይሆንልኛል (፪x)
በዓለም ካለው ነገር ሁሉ በልጦብኛል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔ መርጨዋለሁ ምንም ሳላቅማማ
ዛሬ እፎክራለሁ ጠላት እየሰማ
ቁጥር 5 · Verse 5
የመኖር ትርጉሙ ፍጹም ግራ ገብቶኝ (፪x)
ሌት ተቀን ስጨነቅ የማደርገው ጠፍቶኝ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ከእለታት አንድ ቀን ኢየሱስ ብቅ አለልኝ
ጨልሞ የነበረው ተስፋዬም በራልኝ
እንደቀድሞ እንደኔ ግራ የተጋባችሁ
ነግቶ ሳለ ቀኑ የጨለመባችሁ
ወደ ጌታ ኢየሱስ እኔ ልጋብዛችሁ
እና በእርሱ ብርሃን ብርሃን ታያላችሁ
አዝማች · Chorus
እስከዛሬ ጌታ ሰርተሃል
ቁጥር 7 · Verse 7
ከንግዲህስ ቢሆን ምን ይሳንሃል
ቁጥር 8 · Verse 8
እኔ በአንተ ተስፋ አልቆርጥም
በጠላቴ ዛቻ ከቶ አልናወጥም
የኤርትራን ባህር በክንድህ ከፍለሃል
ፈረሱን ፈረሰኛውን በባሕር ጥለሃል
ዛሬም በእኛ ዘመን ክንድህ ስላልዛለ
የጠላትን ስራ ታፈራርሳለህ
አዝማች · Chorus
እስከዛሬ ጌታ ሰርተሃል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ