ይወጣል
Yewetal
2006 · ትራክ 11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከእግዚኣብሔር ጋር የሆነውን ሰው ማን ይረታል? ኦሆሆ
ማን ይረታል? ኦሆሆ ማን ይረታል? ኦሆሆ
በድል ወጥቶ በድል ይገባል ያሸንፋል ኦሆሆ
ያሸንፋል ኦሆሆ ያሸንፋል ኦሆሆ
ጌታ ከእርሱ ጋር የሆነ ሰው ኦሆሆ
ይወጣል ይወርሳል ያስወርሳል (፬x) ኦሆሆ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁለቱ ብቻ ተለይተው ከአሥሩ
የዕምነት ቃል በድፍረት ሲናገሩ
መውረስ ብቻ ነበር የሚታያቸው
እንውጣና እንውረስ ነው ቋንቋቸው
እንዲሁ እንዳሉት ሆነላቸው
እግዚኣብሔርም ተስፋቸውን አስወረሳቸው
እንደ ካሌብ ኦሆሆ እንደ ኢያሱ
እኔንም አርገኝ ጌታዬ እንደነርሱ
ቁጥር 2 · Verse 2
የእግዚኣብሔር ሰው ሽንፈትን አያወራም
በሚሰማው በሚታየው አይፈራም
የፊቱን ሊይዝ የኃላውን ይረሳል
ቃል ስላለው የረገጠውን ይወርሳል
እርሱማ ከሰው ሁሉ ይለያል
እግዚኣብሔር ያየውን ብቻ ያያል
ፊት ለፊት ገጥሞ ኦሆሆ ከጠላቱ
ባለድል እርሱ ይሆናል በጦርነቱ
የእግዚኣብሔር ሰው ሲናገር ያስተውላል
መልካም ነገር አድሮ ሲያስብ አድሮ ይውላል
ዋዘኞችን ፌዘኞችን ይጠላል
ለያዘው ዕውነት እስከ ሞት ይጨክናል
እሱማ ነው የአስተዋይ ባልንጀራ
ዕውነት ብቻ በአፍ የሚያወራ
ለራዕዩ ዋጋ ይከፍላል ይለፋል
በዘመኑም ቁምነገር ሠርቶ ያልፋል
አዝማች · Chorus
ምሣሌ ሆኖ ኦሆሆ ለሰው ሁሉ
በድል ይወጣል ይገባል ታምኖ በቃሉ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ