Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተመስገን

Temesgen

2006 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያደረግኸውን ሁሉ ሥራህን እያየሁ

እንዴት ዝም እላለሁ (፪x)

ላመስግን እንጂ አንተን ጌታ ሆይ ከልቤ

ቅኔ እየተቀኘሁ (፪x)

ተመስገን ልበልህ ጌታ ኢየሱስ (፪x)

ተባረክ ልበልህ ጌታ ኢየሱስ (፪x)

ተወደስ ልበልህ ጌታ ኢየሱስ (፪x)

ዛሬም ልበልህ ተመስገን

ነገም ልበልህ ተመስገን

ሁሌም ልበልህ አምላኬ ተመስገን

ጌታ ሆይ እድሜን መቁጠር በአንተ ነው አውቃለሁ

በዚህ እደነቃለሁ (፪x)

ምህረትህ ለኔም በዝቶ ዛሬን አይቻለሁ

ላመልክህ ችያለሁ ላከብርህ ችያለሁ

አምላኬ አንተን ይዤ ትልቅ ሰው ተባልኩኝ

ባንተ ተከበርኩኝ (፪x)

ያልነበረኝን ሹመት ማዕረግ አግኝቻለሁ

እኔም ወግ አየሁኝ (፪x)

ጥሩ ስም ሰጥተኸኛል መልካም ሰው አርገኸኛል

እግዚኣብሔር ውለታ ውለህልኛል

ኦ ምስጋናዬን ላብዛብህ (፫x)

አሜን ምስጋናዬ ይብዛልህ (፫x)

ጥጋቤነህ ኩራቴ ነህ ትምክህቴ ነህ

ልጠግብም ባመልክህ

ኢየሱሴ ሌላ ምን ልበልህ

ተባረክ ተወደስ ክበር ከፍ በል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ