እግዚኣብሔርን መፍራት
Egziabhieren Mefrat
2006 · ትራክ 3 · አማርኛ
እግዚኣብሔርን መፍራት ጥበብ ነው የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ
ከሃጢያት መራቅ ማስተዋል ነው ሃሌሉያ
እግዚኣብሔርን የሚፈራ እጅግ ብዙ ደስታ ያያል
በምድር ላይ እድሜው ይረዝማል በበረከት ይኖራል
አይራብም እርሱ ከቶ እግዚኣብሔር ጥጋብ ይሆነዋል
በመከራ ዘመን አይሰጋም ጌታ በድል ያሳልፈዋል
እንዴት የእግዚኣብሔር ፊት ሃጥያት እሰራለሁኝ ብሎ
እግዚኣብሔርን ፈርቶ ዮሴፍ ሸሸ ከሃጥያት ኮብልሎ
እየጨመረ ቢሄድም ፈተናው ቢሆን ያየለ
አምላኩ ሲያስበው ከበር መች ቀረ እንደተጣለ
እግዚኣብሔርን በመፍራቱ የገባ ከእግዚኣብሔር እይታ
በምድር ላይ ቅን ሰው የተባለ ለጠላቱ ያልተረታ
እዮብም ታስቦአል በጊዜው በመከራው ሁሉ ታግሶ
ከሳሹን አሳፈረለት ጌታ ምርኮውን መልሶ
የሰው ልጅ ጥበብን ለማግኘት በዘመኑ ሁሉ ይደክማል
ጥበብ ግን እግዚኣብሔር መሆኑን ያወቀ ከርሱ ጋር ይስማማል
ዘመኑን በተድላ ሊጨርስ የሚፈልግ እግዚኣብሔርን ይፍራ
በመውጣት በመግባቱ ሁሉ ያክብረው በየትኛውም ስፍራ
እንደቀደሙቱ ሐዋሪያት ላንተ እንደተሰጡ ነቢያት
እኔንም ቁምነገረኛ ሰው ለማድረግ ሕይወቴን ቀደሰው
ጌታዬ በሰጠኸኝ መክሊት ነግጄበት ቀንና ሌሊት
ለመጨረሻው ቀን ሽልማት በድል አዘጋጀኝ የኔ አባት
አዝማች · Chorus
ታማኝ ባሪያ አድርገኝ ጌታዬ
እንዲፈጸም ባንተ ደስታዬ
ታማኝ ባሪያ አድርገኝ ኢየሱሴ ይህን ትሻለች ካንተ ነፍሴ
እንደ ዳዊት በኔ ሕይወት ሰልፉን ቢያበዛብኝም ጠላት
መንገዴን ለአንተ አደራ ብዬ እንድጛዝ እርዳኝ አባብዬ
ፍጹም ሳልታጣ ከፊትሕ ይፈጸም በሕይወቴ ሃሳብህ
አምላኬ በዚህ ክፉ ዘመን እርዳኝ ለቤትህ እንድታመን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ